Author: Editorial Team

5th week after Easter (5ተኛ እሑድ አርአየ ሥልጣኖ)

Complete services was streamed via YouTube and Facebook on May 17th, 2020. Click the YouTube link for detail:

Sunday May 17th 2020 the 5th Sunday after Easter service.

The Sermon on this day was based John 21 Ver. 1 – 18

ዮሐንስ 21፡1 ከዚህ በኋላ ኢየሱስ በጥብርያዶስ ባሕር አጠገብ ለደቀ መዛሙርቱ እንደ ገና ተገለጠላቸው፤ እንዲህም ተገለጠ። ስምዖን ጴጥሮስና ዲዲሞስ የሚባለው ቶማስ ከገሊላ ቃና የሆነ ናትናኤልም የዘብዴዎስም ልጆች ከደቀ መዛሙርቱም ሌሎች ሁለት በአንድነት ነበሩ። ስምዖን ጴጥሮስ። ዓሣ ላጠምድ እሄዳለሁ አላቸው። እነርሱም። እኛም ከአንተ ጋር እንመጣለን አሉት። ወጥተውም ወደ ታንኳይቱ ገቡ በዚያችም ሌሊት ምንም እላጠመዱም።

Fourth week after Easter (በ4ተኛ እሑድ) መዝሙር ተንሥአ ወእንስእ ኲሎ ሙታነ።

Full Kidan and Kidase services streaming via YouTube and Facebook on May 10th, 2010

Kidan and Kidase services held on May 10th, 2020

Sermon was delivered, Gospel Luke 24 Ver. 33 – 45.

ሉቃስ 24፡33-34 በዚያችም ሰዓት ተነሥተው ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፥ አሥራ አንዱና ከእነርሱ ጋር የነበሩትም። ጌታ በእውነት ተነሥቶአል ለስምዖንም ታይቶአል እያሉ በአንድነት ተሰብስበው አገኙአቸው። 35 እነርሱም በመንገድ የሆነውን እንጀራውንም በቈረሰ ጊዜ እንዴት እንደ ታወቀላቸው ተረኩላቸው። 36 ይህንም ሲነጋገሩ ኢየሱስ ራሱ በመካከላቸው ቆሞ። ሰላም ለእናንተ ይሁን አላቸው። 37 ነገር ግን ደነገጡና ፈሩ መንፈስም ያዩ መሰላቸው። 38 እርሱም። ስለ ምን ትደነግጣላችሁ? ስለ ምንስ አሳብ በልባችሁ ይነሣል? 39 እኔ ራሴ እንደ ሆንሁ እጆቼንና እግሮቼን እዩ፤ በእኔ እንደምታዩት፥ መንፈስ ሥጋና አጥንት የለውምና እኔን ዳስሳችሁ እዩ አላቸው።

“ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል” (ሉቃ.፩፥፵፰)

ዲያቆን ልሳነጽድቅ ኪዳነ

ስለ እመቤታችን ምሥጋና በአግባቡ ለመረዳት ቅዱሳት መጻሕፍት በሰከነ አእምሮ ከማጥናት እና ከማንበብ ባለፈ ድንግልን ለማመስገን የመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ መሠረት መሆኑ የታወቀ ነው። ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው›› (ሮሜ፡፰፥፬) እንዳለው ያለ መንፈስ ቅዱስ መሪነት ማንኛውም ተግባር ማከናወን እና የተቃና እውነተኛ ሕይወት መምራት አይቻልም፡፡

በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ሕይወትን መምራት የእግዚአብሔር ልጅ የመሆን ምልክት ነው፡፡ ለእመቤታችን ምስጋና፣ ስግደት ስለ ማቅረብ ስለ አማላጅነቷ እንዲሁም ክብሯን ለመቀበል የሚታወኩትን ስንመለከት ከአእምሮ በላይ የሆነውን የመንፈስ ቅዱስ አሠራርን አለማስተዋላቸውንና የእግዚአብሔር ልጆች አለመሆናቸውን እንረዳለን፡፡ እመቤታችንን ለማመስገን የመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ረዳትነት እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ ያለ መንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ቅድስት ድንግል ማርያምን ማመስገን አይቻልም፡፡

ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም ‹‹የነቢያት ትንቢታቸው የሐዋርያት ዜናቸው አንቺ ነሽ›› ያላትን እመቤታችንን አበው በሱባኤያቸው መልስ ያገኙባትን አለመቀበል  የአእምሮ ይቡስነት (ድንቁርና) ተጭኖታል ከማለት ውጭ ምን ማለት ይቻላል፡፡ (ውዳሴ ማርያም ዘማክሰኞ ፮)

ቅዱሳት መጻሕፍት በመተባበር የሚመሠክሩት እመቤታችንን ለማመስገን የመንፈስ ቅዱስ ረድኤት አስፈላጊ ስለ መሆኑ ነው፡፡ ለዚህም በአጭሩ ሁለት ምስክርነት ማለትም ከሰማያውያን ቅዱሳን ቅዱስ ገብርኤል እና ከምድራውያን የቅድስት ኤልሳቤጥ ምስክርነት እናያለን፡፡

ቅዱስ ገብርኤል የተላከው ከእግዚአብሔር ለመሆኑ እያንዳንዱ ያቀረበው ምስጋናና አክብሮት ምስክር ነው፡፡ ቃሉም የሚለው ‹‹ወበሳድስ ወርኀ ተፈነወ ገብርኤል መልእክ እምኀበ እግዚአብሔር፤ በስድስተኛው ወር ገብርኤል መልአክ ከእግዚአብሔር ተላከ›› ….የተላከው  ብርሃናዊ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ወደ እርሷ ገብቶ እየወደቀ እየተነሳ ክብርት ልዕልት ንጽህት መሆኗን እና ስለ ተሰጣት ጸጋ ተጠንቅቆ በቅደም ተከተል የተናገረው እንዲህ በማለት ነበር ‹‹ደስ ይበልሽ ጸጋ የሞላብሽ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ›› አላት፡፡ (ሉቃ. ፩፥፳፰-፳፱)

ሌላ ምስክርነት ደግሞ ቅድስት ኤልሳቤጥ ለእመቤታችን ያቀረበችው ምስጋና ነው፡፡ ስለ ድንግል ማርያም እና ስለ ልጇ ወዳጅዋ የመሰከረችው በመንፈስ ቅዱስ ተመርታ ነበር። ይህም ቅዱስ ሉቃስ በወንጌሉ እንዲህ በማለት ምስክርነቱን ይሰጣል ‹‹ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ ጽንሱ በማሕጸኗ ውስጥ  በደስታ ዘለለ፤ በኤልሳቤጥም መንፈስ ቅዱስ ሞላባት››።  ድምጿን አሰምታ እንዲህ አለች ‹‹አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ  ነሽ፤ የማኅጸንሽም ፍሬ የተባረከ ነው። የጌታየ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል? እነሆ የሰላምታሽ ድምጽ በጆሮየ በመጣ ጊዜ ጽንሱ በማኅጸኔ በደስታ ዘልዋልና››። ከጌታ የተነገረላት ቃል ይፈጸማል እና ያመነች ብጽዕት ናት። (ሉቃ.፩፥፵፩-፵፮)

የፅንሱ በማኅፀን መዝለል እና ማመስገን፣ የቅዱስ ገብርኤል የምስጋና አቀራረብና ምስክርነት እንዲሁም እመቤታችን እና የመልአኩ ቃለ ተዋስኦ  ምስጋናዋ ከእግዚአብሔር ስለ መሆኑ በቂ ማሳያ ነው፡፡ እመቤታችንም ‹‹ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል›› ማለትም ትውልደ ሴም፣  ትውልደ ያፌት  እና ትውልደ ካም ያመሰግኑኛል ብላለች። (ሉቃ.፩፥፵፰)

ከእግዚአብሔር የተላከ ብርሃናዊ መልአክ ካመሰገናትና በመንፈስ ቅዱስ የተቃኘች ቅድስት ኤልሳቤጥ ካወደሰቻት በማኅፀን ያለ ፅንስም በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ ከሰገደ ዛሬም  እመቤታችንን ማመስገን የእግዚአብሔር ልጅ መሆንና ጸጋ መንፈስ ቅዱስ የመቀበል አንዱ ምልክት ነው፡፡ እመቤታችን አለማመስገን ከእግዚአብሔር ልጅነት መውጣት ነው፡፡ ምክንያቱም እርሱ እግዚአብሔር የተቀበላቸውን እና ያከበራቸውን አለመቀበል እንዲሁም አለማክበር የእግዚአብሔርን ፍቃድ አለመፈጸምና እግዚአብሔርን አለማክበር ነው፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም እንዲህ ነበር ያለው ‹‹እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል›› (ማቴ. ፲፥፵)

ስለዚህም እመቤታችንን ማመን ማለት ክብሯን ንጽህናዋን፣ ቅድስናዋን እና ምስጋናዋን መቀበል ማለት ነው፡፡ ለዚህም እንደ ማሳያ የምናየው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል  የሚከተለው ይሆናል። በኦሪት ዘጸኣት እንደምንመለከው ‹‹በዚያን ቀን እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ከግብጻውያን እጅ አዳናቸው ፤…እግዚአብሔር በእንዴት ያለ  ታላቅ ኃይል ግብጻውያንን እንዳሸነፈ እስራኤላውያን ባዩ ጊዜ  እግዚአብሔርን ፈሩ በእግዚአብሔር እና በሙሴ አመኑ›› አሁን እስራኤላያን በሙሴ እና በእግዚአብሔር አመኑ ተብሎ መጸፉ እስራኤላውያን ሙሴ እና እግዚአብሔርን አስተካክለው አመለኩ እንዲሁም ሙሴን እንደ እግዚአብሔር አዩት ማለት አይደለም። አስራኤላውያን በእግዚእብሔር ያመኑበት ማመን እና በሙሴ ያመኑበት ማመን የተለየ መሆኑ አስተዋይ ሰው ልብ ይለዋል። (ዘጸ. ፬፥፩ ፤ ዮሐ. ፭፥፮)

እመቤታችን ድንግል ማርያምን የምናመሰግናት ስለተሰጣት ጸጋ እና ክብር ነው። የተሰጣት ክብር ደግሞ ከጸጋ ባለቤት  ከልዑል እግዚአብሔር መሆኑን  አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ  በመጽሐፈ ምሥጢር ላይ እንዲህ ይላል ‹‹ስለ ተሰጣትም የእግዚአብሔር ጸጋ የሔዋን መርገም በእርሷ ላይ ተቋረጠ  እንዲህ ያለ ስጦታ  ለአዳም እና ለዘሩ እስከ ዘለዓለም ለሌላ አልተሰጠም።›› በዚህ ብቻ ሳይሆን ስለ ንጽሕኗዋ፣ ስለ ቅድስናዋ ጭምር ምስጋና እናቀርባለን።

ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም እመቤታችንን ከመውደዱ የተነሳ እመቤቴ ምስጋናዋ እንደሰማይ ኮከብ እንደ ምድር አሸዋ በዝቶልኝ እንደ ልብስ ለብሼው እንደ ምግብ ተመግቤው ጠግቤ እያለ ሲመኝ ይኖር ነበረ። የሚሹትን መግለጽ ለእግዚአብሔር ልማዱ ነውና፤ ገልጾለት * ከአራት ሺህ በላይ ድርሰት ደርሷል። አኃዝ እግዚኦ መዋግደ ጸጋከ እስኪል ድረስ ። ሊቁ ያቀረበው ምስጋና መነሻው መንፈስ ቅዱስ እንደነበረ የሚከተለውን የአበው ትርጉም እንመልከት፡። “የነግህ ተግባሩን  አድርሶ ከመካነ ግብሩ ተቀምጦ ሳለ  እመቤታችን ትመጣለች የብርሃን ምንጣፍ ይነጠፋል፤ የብርሃን ድባብ ይዘረጋል። በዚያም ላይ ሁና ሰላም ለከ ኦፍቁርየ  ኤፍሬም ትለዋለች፤ እርሱም ታጥቆ  እጆ ነሥቶ ይቆማል። ወድሰኒ ትለዋለች፤ እፎ እክል ወዶሶኪ ዘኢይክሉ ሰማያውያን ወምድራውያን። ምድራውያን ጻድቃን ሰማዕታት ሰማያውያን መላእክተ  አንቺን ማመስግን የማይቻላቸው ለእኔ እንደምን ይቻለኛል አላት። በከመ አለበወከ መንፈስ ቅዱስ ተናገር፤ መንፈስ ቅዱስ እንዳናገረህ ተናገር አለችው። በተረቱበት መርታት ልማድ ነውና …ከዚህም በኋላ ባርክኒ ይላታል፤ በረከተ ወልድየ ወአቡሁ መንፈስ ቅዱስ  ይኅድር በላዕሌከ ትልዋለች  ተባርኮ ምስጋናዋን ይጀመራል።

ስለ እመቤታችን ምስጋና እኛ ሊቁን ተከትለን “ብጽዕት አንቲ ኦ እግዝእትነ ማርያም ወላደተ አምላክ፤ አምላክን የወለድሽ እመቤታችን ሆይ ንዕድ ነሽ ክብር ነሽ። እስመ ብዓንኪ ዘአልቦ ትርጓሜ። ለምስጋናሽ ምሳሌ የለውምና። በማለት ክብሯን፣ በምስጋናዋን ከማግነን ሌላ ምን እንላልን። ሰው ሁኖ ካዳነን ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኚል እያለን የባሕርያችን መመኪያ ድንግል ማርያምን በማመስገን እና በመማጸን በርትዕት ተዋሕዶ ሃይማኖታችን ጸንተን ለመኖር ያብቃን፤ አሜን፡፡

ፀሐይን ያጨለመ ፀሐይ

ጌታችን በሮማውያን እጅ ዕርቃኑን በተሰቀለበት ዕለት ከቀኑ በስድስት ሰዓት ላይ ታላቋ የእሳት ኳስ ብርሃናዊቷ ፀሐይ ድንገት ጨለመች፤ ጨረቃም ደም መሰለች፤ ከዋክብትም ረገፉ (ጨለሙ)። በነቢዩ ሚልክያስ ‹‹ስሜን ለምትፈሩ ለእናንተ የጽድቅ ፀሐይ ትወጣላችኋለች፤ ፈውስም በክንፎችዋ ውስጥ ይሆናል›› ተብሎ በትንቢት የተነገረለት እውነተኛው ፀሐይ ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ እጆቹን እንደ ክንፍ በዘረጋ ጊዜ በእውነተኛው ፀሐይ ፊት ማብራት ያልተቻላት ፀሐይ በድንገት ጨለመች። (ሚል. ፬፥፪) በመዞር ምክንያት የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ የሌለበት፣ ለሁሉ የሚያበራው እውነተኛው ብርሃን ክርስቶስ በመስቀል ላይ እንደተሰቀለ ባየች ጊዜ ታናሽዋ ፀሐይ ብርሃንዋን ከለከለች።

ማንነቱን ያልተረዱት አይሁድ ዕርቃኑን ሰቅለው እያዩ ሊዘብቱበት ሲቆሙ ፍጥረታቱ ግን አምላካቸው ተሰቅሎ አይተው መቋቋም ተሳናቸው፤ ስለ ጌታችን ሥቃይ ምድርን በኀዘን አጨለሟት፣ ስለ ጌታችን ደም መፍሰስ ጨረቃ ደም መሰለች፤ ሰዎች በፈጣሪ ፊት ስላሳዩት ድፍረት የሰዎች መገኛ የሆነችው ምድር ተንቀጠቀጠች፣ ሰውነቱ በግርፋት መሰንጠቁን አይተው ዓለታትም ተሰነጣጠቁ። ‹‹ፍጥረታት ሁሉ በሥቃዩ አብረውት ተሠቃዩ፤ ሲሰቀል እንዳታየው ፀሐይ ፊትዋን ሸሸገች። ከእርሱ ጋር አብራ ልትሞት ብርሃንዋን አጠፋች፤ ለሦስት ሰዓታት ጨለማ ከሆነ በኋላ ግን መልሳ አበራች፤ ይህም በሦስተኛው ቀን እንደሚነሣ  ስትመስክር ነው›› ይላል ቅዱስ ኤፍሬም።

              የሰማይ ብርሃናት የመጨለማቸው ምክንያት የጌታችንን ዕርቃኑን እነርሱ በብርሃናቸው አይተው ለሌላው ላለማሳየት ነው። አባ ጊዮርጊስ ‹ፀሐይ ጸልመ፤ ወወርኅ ደመ ኮነ፤ ወከዋክብት ወድቁ ፍጡነ፤ ከመ ኢይርአዩ ዕርቃኖ ለዘአልበሶሙ ብርሃነ › ‹ፀሐይ ጨለመ፤ ጨረቃም ደም ሆነ፤ ከዋክብትም ፈጥነው ወደቁ፤ ብርሃንን ያለበሳቸውን አምላክ ዕርቃኑን እንዳያዩ› በማለት እንደዘመረው በብርሃን ያስጌጣቸውን የፈጣሪን ዕርቃኑን ላለማየት (ማሰብ የማይችሉት ፍጥረታት በብርሃናት ላይ በተሾሙ መላእክት እጅ) ብርሃናቸውን ሠወሩ።

ጻድቁ ኖኅ የወይን ጠጅን ጠጥቶ በሰከረና ዕርቃኑን በሆነበት ዕለት ልጁ ካም ዕርቃኑን እያየ ሲዘብትበት ሴምና ያፌት የተባሉት ልጆቹ ግን የአባታቸውን ዕርቃን ሸፍነው ነበር። (ዘፍ. ፱፥፳፩‐፳፫) እንደ ኖኅ በጠጅ ሳይሆን በሰው ልጅ ፍቅር ሰክሮ ዕርቃኑን በመስቀል ላይ የተሰቀለውን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስንም አይሁድ እንደ ካም ሲዘብቱበት፤ ፀሐይ፣ ጨረቃና ከዋክብት ግን እንደ ሴምና ያፌት ዕርቃኑን ሸፈኑለት።    

              ነቢያቱ አስቀድመው ስለዚያ የቀትር ጨለማ ትንቢቶችን ተናግረው ነበር። በነቢዩ ዘካርያስ ‹‹አንድ ቀን ይሆናል፤ እርሱም በእግዚአብሔር ዘንድ የታወቀ ይሆናል፤ ቀንም አይሆንም ሌሊትም አይሆንም፤ ሲመሽም ብርሃን ይሆናል›› ተብሎ ተጽፎ ነበር። (ዘካ. ፲፬፥፯) በእርግጥም አንድ ቀን የተባለው ዕለተ ዓርብ ነው። ‹ቀንም አይሆንም ሌሊትም አይሆንም› ያሰኘው የሦስት ሰዓታቱ ጨለማ ነው። ቀን እንዳይባል ጨልሟል፤ ሌሊት እንዳይባል ደግሞ ከቀኑ ስድስት ሰዓት ነው። ሲመሽ ብርሃን ይሆናል የተባለው ደግሞ ከዘጠኝ ሰዓት በኋላ ብርሃኑ ስለተመለሰ ነው።

ከደቂቀ ነቢያት በአንዱ በአሞጽ አንደበት ደግሞ እግዚአብሔር እንዲህ ተናግሮ ነበር ፡- ‹‹በዚያ ቀን ፀሐይ በቀትር እንድትገባ አደርጋለሁ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ በብርሃንም ቀን ምድሩን አጨልማለሁ፤ ዓመት በዓላችሁንም ወደ ልቅሶ ዝማሬያችሁንም ወደ ዋይታ እለውጣለሁ፤ እንደ አንድያ ልጅም ልቅሶ ፍጻሜውንም እንደ መራራ ቀን አደርገዋለሁ›› (አሞ. ፰፥፱‐፲) ይህም ስለ ዕለተ ዓርብ የተነገረ ነበር። የዓመት በዓላቸው ፋሲካ በሚከበርበት ዕለት ፀሐይ ጨለመች፤ የኢየሩሳሌም ሴቶች ልቅሶም የትንቢቱ መፈጸሚያ ሆነ እግዚአብሔር ይህንን የተፈጥሮ ምላሽ የፈቀደው አይሁድ አምላክነቱን ተረድተው ከክፉ መንገዳቸው እንዲመለሱ ጥሪ ለማድረግ ነበር። ለቁጣ ቢሆን ኖሮ ሁሉንም መሬት ተሰንጥቃ እንድትውጣቸው ለማድረግ ይቻለው ነበር። እርሱ ግን ‹‹ፀሐይን አጨለመ፤ ገዳዮቹን ግን አልተቀየመም›› ‹‹ፀሐይኒ አጽለመ፤ ወቀታሊያነ ኢተቀየመ›› (ግብረ ሕማማት ዘዓርብ ፮ ሰዓት) የሚያሳዝነው ግን የሰቀሉት አይሁድን ‹ተፈጥሮ እንኳን› አላስተማራቸውም፤ ‹‹ሰማያውያን እርሱን እንዳያዩ ፊቱን ሸፈኑ ምድራውያን ግን ምራቃቸውን ይተፉበት ነበር›› መሬት ፈርታ ስትንቀጠቀጥ አይሁድ ግን አልተንቀጠቀጡም፤ ‹‹ዓለት ተሰነጠቀ፤ የዐመፀኞቹ ልብ ግን አልተመለሰም›› ልባቸው ከዓለት ይልቅ የደነደነ ነበር። በዚያች በዕለተ ዓርብ ከነበረው መነዋወጥ የተነሣ ዓለም ልታልፍ ትችል ነበር። ቸርነቱ የበዛው አምላክ ‹‹ምድርን ያለ ጊዜዋ እንዳታልፍ አጸናት፤ ደሙን በምድር ላይ አፈሰሰ፤ ከኅልፈት ጠበቃት በእርስዋ ያለውንም ሁሉ ጠበቀ››

በዕለተ ዓርብ ከተፈጸሙት ተአምራት ሁሉ ግን እጅግ አስደናቂው ተአምር የሰው ልጅ መዳኑ ነው። ከፀሐይ መጨለምና ከጨረቃ ደም መምሰል በላይ የእኛ የጨለመ ማንነታችንን ብሩሕ ማድረጉ፣ ከቤተ መቅደስ መጋረጃ መቀቀድ በላይ በሰውና በእግዚአብሔር መካከል የነበረው የጥል ግድግዳ መፍረሱ፣ ከሙታን ከመቃብር መውጣት በላይ የሰው ልጆች ከሲኦል መውጣቱ፣ የክርስቶስ የደሙ ጠብታ ዓለምን ከኃጢአት ማጠቧ እጅግ አስደናቂዎቹ የመስቀል ላይ ተአምራት ናቸው። ቅዱስ ያሬድ ‹‹ምድር በክርስቶስ ደም ታጥባ ፋሲካን ታደርጋለች›› (ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ) በማለት ስለዚህ ተአምር ዘምሯል።

በሦስቱ ሰዓታት ውስጥ ስለነበረው ስለ ሰማይ ብርሃናት ሁኔታ በወንጌላት የተጻፈው የፀሐይ መጨለም ብቻ ሲሆን ስለ ጨረቃ ደም መሆንና ስለ ከዋክብት መጨለም በወንጌላቱ ውስጥ አልተመዘገበም። ነቢያቱና ሐዋርያቱ ግን ዕለተ ዓርብን ከዕለተ ምጽዓት በሚያስተባብሩ ትንቢቶቻቸውና ትምህርቶቻቸው የጨረቃና የከዋክብትን ነገርም መዝግበውልናል።

‹‹ፀሐይና ጨረቃ ጨልመዋል፤ ከዋክብትም ብርሃናቸውን ሰውረዋል፤ እግዚአብሔርም በጽዮን ሆኖ ድምፁን ከፍ አድርጎ ይጮኻል›› (ኢዮ. ፫፥፲፭)

‹‹ምድሪቱ በፊታቸው ትናወጣለች፤ ሰማያትም ይንቀጠቀጣሉ፤ ፀሐይና ጨረቃም ይጨልማሉ፤ ከዋክብትም ብርሃናቸውን ይሰውራሉ›› (ኢዮ. ፪፥፲)

‹‹የሰማይ ከዋክብትና ሠራዊቱ ብርሃናቸውን አይሠጡም፤ ፀሐይም በወጣች ጊዜ ትጨልማለች፤ ጨረቃም በብርሃኑ አያበራም›› (ኢሳ. ፲፫፥፲)

    ቅዱስ ጴጥሮስ በሦስት ሺህ ሰዎች ፊት ባስተማረበት በዕለተ ጰራቅሊጦስም የነቢዩ ኢዮኤልን ትንቢት ሲጠቅስ ‹‹ታላቅ የሆነ የተሰማም የጌታ ቀን ሳይመጣ ፀሐይ ወደ ጨለማ ጨረቃም ወደ ደም ይለወጣሉ፤ የጌታን ስም የሚጠራም ይድናል›› በማለት ተናግሯል። (ሐዋ. ፪፥፳‐፳፩) ይህ ትንቢት በዕለተ ዓርብ በፀሐይና ጨረቃ የተፈጸመ ሲሆን ‹የጌታን ስም የሚጠራ ይድናል› የሚለው ቃል ደግሞ ከጌታ ቀኝ በተሰቀለው ወንበዴ መዳን ተፈጽሟል፡፡ ነቢዩ ኢዮኤል ስለ ዕለተ ምጽዓት የተናገረውን ይህን ትንቢት ቅዱስ ጴጥሮስ ጠቅሶ ማስተማሩም በዚያ ለተሰበሰቡት አይሁድ በዕለተ ዓርብ የተፈጸሙትን ተአምራት በማስታወስ ባለማመናቸው ከጸኑ ሊመጣባቸው የሚችለውን እንዲገምቱ ሲያመለክት እንደሆነ ሊቃውንት ያብራራሉ።

በዕለተ ዓርብ የተከሰተውን የፀሐይን መጨለም በየዘመናቱ የተካነ ጥበብ ነበር። የግሪካውያን ፍልስፍና እጅግ የመጠቀውና ለብዙ የሳይንስ ዘርፎች ስም አውጪ የሆነው አዳዲስ አሳቦች ተከብረው የሚሰሙበት እንዲህ ያለ ሥፍራ የውይይት ቦታ ከጥንት ስለነበረ ነው። ቅዱስ ጳውሎስ ሲሰብክ ሰምተው ወዲህ ሲያመጡት በአርዮስፋጎስ ከተሰበሰቡት ሊቃውንት መካከል የፍርድ ቤት ዳኛ የነበረው ዲዮናስዮስም ተገኝቶ ነበረ። በዚያን ቀን እነዚያ ፈላስፎች ከጳውሎስ ጋር ብዙ ክርክሮችን አድርገው ግማሾቹ ሲያፌዙበት ግማሾቹ ግን በክርስቶስ አመኑ።

 በሐዋርያት ሥራ ላይ እንደተጻፈው ቅዱስ ዲዮናስዮስ ካመኑት ጥቂት ሰዎች አንዱ መሆን የቻለ ሲሆን ‹በክርስቶስ አምላክነት አምኜያለሁ› ያለውም መዝግቦ ያስቀመጠው ፀሐይ የጨለመችበት ዕለት መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ የተሰቀለበት ዕለተ ዓርብ መሆኑን ከቅዱስ ጳውሎስ ጠይቆ በማረጋገጡ ነበር። የፀሐይ መጨለም ዓለም አቀፍ ክስተት በመሆኑ ምክንያት ቤተ ክርስቲያናችን የብዙ ድርሰቶች ጸሐፊ የሆነውን ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ዲዮናስዮስን ዘአርዮስፋጎስን አገኘች። አስደናቂዋ ፀሐይ ለዲዮናስዮስ ጨልማ  አበራለችለት!!    

ሕማማት ገፅ 400

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

Timket Celebration

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን

ክቡራንና ክቡራት ይህንን መንፈሳዊና የጥምቀት ዓመታዊ በዓል ለማክበር የታደማችሁ የልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቦች የእናታችን የቅድስተ ቅዱሳን የንጽሕት ድንግል ማርያም የአሥራት ልጆች በቅድሚያ እንኴን ለ 2010 ዓ/ም ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት በሰላም አደረሳችሁ።

“ሖረ ኢየሱስ አምገሊላ ኀበ ዮሐንስ ከመ ያጥምቆ በፈለገ ዮርዳኖስ ” ማቴ 313

የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ በዓለ ጥምቀት ከበዓለ ልደት ቀጥሎ የሚከበር ዓቢይ በዓል ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ይህንን በዓል ታቦታተ ሕጉን ይዛ ከቅጽረ ቤተክርስቲያን ወጥታ በዝማሬ እና በእልልታ በሜዳ በወንዝ ዳር የምታከብረው ያለምክንያት አይደለም። ከላይ በርእሱ እንደተገለጸው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐንስ እጅ ይጠመቅ ዘንድ ከገሊላ አውራጃ ከናዝሬት ከተማ ወደ ይሁዳ አውራጃ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ መጥቶ መጠመቁን አብነት መሠረት በማድረግ ነው። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐንስ እጅ በዮርዳኖስ ለምን ተጠመቀ ?

ይህ ጥያቄ ብዙ ምሥጢር ያለው ቢሆንም ባጭሩ ለመግለጽ ክብር ይግባውና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃጢያት ኖሮበት ሳይሆን፤

  • በነቢያት የተነገረውን ትንቢት ለመፈጸም
  • ውሃውን ለመቀደስ
  • የአዳምን እዳ ለመደምሰስ
  • ለጥምቀት ሃይልን ለማሰጠት
  • ለእኛም አርአያና ምሣሌ ለመሆን በዮሐንስ እጅ በፈለገ ዮርዳኖስ ተጠመቀ

1ኛ፤ ከዘመናት በፊት በነቢዮ ዳዊት የተነገረው ትንቢት፤ ይህም ትንቢት “ባሕርኒ ርእየት ወጎየት ወዮ ርዳኖስኒ ገብአ ድኀሬሁ አድባር አንፈርአጹ ከመ ሐራጊት ” ባህር አየች ሸሸችም ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ ተራሮችም እንደ ኮርማዎች ዘለሉ። መዝ 113/114 3-6 በማለት

2ኛ፤ እንደዚሁም በዮሐንስ እጅ መጠመቁ “ወናሁ አነ እፌኑ መልዓክየ ዘይጸይህ ፍኖትየ በቅድመ ገጽከ ” መንገዱን ለማዘጋጀት ቃል ኪዳኑን ለማወጅ እግዚአብሔር አስቀድሞ መልዕክተኛውን ይልካል። ትን ሚል 3፤ 1-3 በማለት የተነገርው ትንቢት ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐንስ እጅ በፈለገ ዮርዳኖስ ተጠምቆ ሲወጣ “ወናሁ ተርኀወ ሰማይ ወርእየ መንፈሰ እግዚአብሔር እንዘ ይወርድ ከመ ርግብ ወይወርድ ላእሌሁ ”  ሰማይ ተከፍቶ መንፈስ ቅዱስ በአምሳለ ርግብ ወርዶ በራሱ ሲቀመጥ መጥምቁ ዮሐንስ አየ እንደዚሁም “ መጽአ ቃል እምደመና ዘይብል ዝንቱ ውእቱ ውልድየ ዘአፈቅር ወሎቱ ስምእዎ ” ለተዋህዶ የመረጥሁት በእርሱ ህልው ሆኜ ልመለክበት የወደድሁት ልጄ ይህ ነው። እርሱን ስሙት የሚል ቃል ከወደ ሰማይ ተሰማ ወንጌላውያኑም በዚህ ምሥጢረ ሥላሴን በግልጽ አስተምረውናል። አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐንስ እጅ ተጠምቆ ከውሃው ሲወጣ የባሕርይ ሕይወቱ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል በራሱ ላይ ሲያርፍ የባሕርይ አባቱ አብም የወደድሁት ልጄ ይህ ነው በማለት በእርሱ ህልው መሆኑን መስክሯል።

በዚይም የባሕርይ አምላክነቱን እና የባሕርይ ልጅነቱን ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ አስመስክሮበታል። ምሥጢረ ሥጋዊ ከሦስቱ አካላት ሁለተኛው አካል ቃለ እግዚአብሔር ወልድ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በሥጋ የመገለጡ አምላክ ሰው ሰው አምላክ የመሆኑ ምሥጢር ነው “ቃል ሥጋ ኮነ ወሃደረ ላእሌነ ” ቃል ሥጋ ሆነ በእኛም አደረ ዮሐ 1፤14 በማለት ሐዋርያው እንዳስተማረን ስለዚህ በምሣሌና በምሥጢር የተገለጸውን ካማጤን ጋር የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ አንድነት እና ሦስትነት የታወቀበት ዕለት መሆኑን ተገንዝበን እምነታችንን አጽንተን እንድንይዝ ያስተምረናል። የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል አከባበር ዋናው ምሥጢር ይህ ነው። እግዚአብሔር አምላካችን በዓሉን የተቀደሰ በዓል ያድርግልን! ለሀገራችን ለቤተ ክርስቲያናችን ለሕዝባችን ሰላምን ፍቅርን አንድነትን ያድለን።

ወስብሐት እግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን

Timket

Timket (Amharic: ጥምቀት which means “baptism”) is the Ethiopian Orthodox celebration of Epiphany will be celebrated in Worcester Kidist Kidane Mehret Ethiopian Orthodox Tewahedo Church on January 20 and 21, 2018. Timkat celebrates is commemoration of the baptism of Jesus in the Jordan River. See detail the celebration time and place from the attached flier.