አብነት ትምህርት ለፓፓሳት፤ ለካህን፤ ለዲያቆን፣ ወይም በቤተክርስቲያን ለሚያገለግሉ ብቻ አይደለም ጠቀሜታው። ትምህርቱም ለተጠቀሱት ብቻ ሳይሆን ሁሉም በክርስቶስ ክርስቲያን የተባለ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ የሆነ ሁሉ ሊያውቅ ይገባል። መጪውን ትውልድ በመገንባት ሂደት ውስጥ ታዳጊ ህጻናት፤ ወጣቶች፤ እንዲሁም በተለያዩ ምክንያት ትምህሩቱን መከታተል ሳይችሉ ለቀሩ ሁሉ፣ ይህ ትምህርት በደብረ መንክራት ቅዱስ ገብርኤል ኢ/ኦ/ተ/ቤ ተዘጋጅቷል።
የአብነት ትምህርት ማለት ከቃሉ ስንረዳ “አብነት” ማለት መሠረት፣ መነሻ፣ መጀመሪያ፣ የሚቀድመው የሌለ የሁሉም የበላይ ማለት ነው። አብነት ትምህርት ቤት ማለት ከአባት የተገኘ ከአበው የተወረሰ ከጥንት የነበረ የማንነት መገለጫ በራስ ቋንቋ በራስ ፊደል በራስ ሥራዓተ ትምህርት የሚሰጥ ከትውልድ ወደ ትውልድ የተላለፈ ትምህርት የሚሰጥበት ትምህርት ቤት ማለት ነው ። የአንድን ሕዝብ የአንድን ሀገር ጥበብ እና ዕውቀት ለዚያ ሕዝብ እና ለዚያች ሀገር ዜጎች የሚያስተምሩበት ትምህርት ቤት ማለት ነው ። ሥርዐተ ትምህርቱ አገር በቀል በሆኑ ብሔራውያን ሊቃውንት ተዘጋጅቷል ። ከጊዜ ወደ ጊዜም ዳብሯል ። የአብነት ትምህርት ቤት በልማድ “የቆሎ ትምህርት ቤት” በመባል በሕዝባችን ዘንድ ይታወቃል ። አንዳንድ ሰዎች ደግሞ “የቄስ ትምህርት ቤት ” እንዲሁም አንዳንዶች ” የቤተ ክህነት ትምህርት ቤት ” ይሉታል ።የመጀመሪያው ልማዳዊ ስያሜ የተማሪዎቹን አመጋገብና የችግር ኑሮ የሚገልጥ እንጅ የትምህርት ቤቱን ማንነት እና ዓላማ የማያሳይ በመሆኑ ተቀባይነት ያለው ስያሜ አይደለም ።
ስለዚህ ለልጆቻችን በጣም አስፈላጊና መንፈሳዊ ሕይወታቸውን የሚለውጥ፤ ከፈጣሪያችን ከእግዚአብሔር ጋር ያለው ግንኙነት የሚያጠናክር፤ በየጊዜው በየዕለቱ፤ አምላካችን እግዚአብሔርን ስሙን ሲጠሩ ምን እያሉ መጽለይ እንዲችሉ ይረዳቸዋል። ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ፤ ሃይማኖታችንን የሚያጠናክር ይሆናል።
በዚህ መሰረት ህጻናት ልጆች መማር በሚችሉበት ቀለል ባለ መልኩ፤ በጽሑፍና በድምጽ በተቀነባበረ መልኩ የተዘጋቸውን ትምህርት ተማሪዎች ይከታተላሉ። በክፍል በክፍል ተከፋፍሎ የተዘጋጀውን ትምህርት፤ መምህሩ ተማሪው ማለፉን ካረጋገጠ በኋላ ወደ ሚቀጥለው የትምህርት ክፍል እንዲቀጥል ያደርገዋል። ሁልጊዜ ተማሪው ያለበት ደረጃ ይታወቃል ማለት ነው።
ይህንንም ለማድረግ ፈጣሪያችን አምላካችን እግዚአብሔር መምህራችንና ተማሪዎቻችንን ባርኮ ትምህርቱን እንዲገልጽላቸው ያድርግልን። አሜን!
Courses you might be interested in
-
0 Lessons
-
0 Lessons
-
0 Lessons
-
0 Lessons