አብነት ትምህርት ለፓፓሳት፤ ለካህን፤ ለዲያቆን፣ ወይም በቤተክርስቲያን ለሚያገለግሉ ብቻ አይደለም ጠቀሜታው። ትምህርቱም ለተጠቀሱት ብቻ ሳይሆን ሁሉም በክርስቶስ ክርስቲያን የተባለ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ የሆነ ሁሉ ሊያውቅ ይገባል። መጪውን ትውልድ በመገንባት ሂደት ውስጥ ታዳጊ ህጻናት፤ ወጣቶች፤ እንዲሁም በተለያዩ ምክንያት ትምህሩቱን መከታተል ሳይችሉ ለቀሩ ሁሉ፣ ይህ ትምህርት በደብረ መንክራት ቅዱስ ገብርኤል ኢ/ኦ/ተ/ቤ ተዘጋጅቷል።

የአብነት ትምህርት ማለት ከቃሉ ስንረዳ “አብነት” ማለት መሠረት፣ መነሻ፣ መጀመሪያ፣ የሚቀድመው የሌለ የሁሉም የበላይ ማለት ነው። አብነት ትምህርት ቤት ማለት ከአባት የተገኘ ከአበው የተወረሰ ከጥንት የነበረ የማንነት መገለጫ በራስ ቋንቋ በራስ ፊደል በራስ ሥራዓተ ትምህርት የሚሰጥ ከትውልድ ወደ ትውልድ የተላለፈ ትምህርት የሚሰጥበት ትምህርት ቤት ማለት ነው ። የአንድን ሕዝብ የአንድን ሀገር ጥበብ እና ዕውቀት ለዚያ ሕዝብ እና ለዚያች ሀገር ዜጎች የሚያስተምሩበት ትምህርት ቤት ማለት ነው ። ሥርዐተ ትምህርቱ አገር በቀል በሆኑ ብሔራውያን ሊቃውንት ተዘጋጅቷል ። ከጊዜ ወደ ጊዜም ዳብሯል ። የአብነት ትምህርት ቤት በልማድ “የቆሎ ትምህርት ቤት” በመባል በሕዝባችን ዘንድ ይታወቃል ። አንዳንድ ሰዎች ደግሞ “የቄስ ትምህርት ቤት ” እንዲሁም አንዳንዶች ” የቤተ ክህነት ትምህርት ቤት ” ይሉታል ።የመጀመሪያው ልማዳዊ ስያሜ የተማሪዎቹን አመጋገብና የችግር ኑሮ የሚገልጥ እንጅ የትምህርት ቤቱን ማንነት እና ዓላማ የማያሳይ በመሆኑ ተቀባይነት ያለው ስያሜ አይደለም ። 

ስለዚህ ለልጆቻችን በጣም አስፈላጊና መንፈሳዊ ሕይወታቸውን የሚለውጥ፤ ከፈጣሪያችን ከእግዚአብሔር ጋር ያለው ግንኙነት የሚያጠናክር፤ በየጊዜው በየዕለቱ፤ አምላካችን እግዚአብሔርን ስሙን ሲጠሩ ምን እያሉ መጽለይ እንዲችሉ ይረዳቸዋል። ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ፤ ሃይማኖታችንን የሚያጠናክር ይሆናል።

በዚህ መሰረት ህጻናት ልጆች መማር በሚችሉበት ቀለል ባለ መልኩ፤ በጽሑፍና በድምጽ በተቀነባበረ መልኩ የተዘጋቸውን ትምህርት ተማሪዎች ይከታተላሉ። በክፍል በክፍል ተከፋፍሎ የተዘጋጀውን ትምህርት፤ መምህሩ ተማሪው ማለፉን ካረጋገጠ በኋላ ወደ ሚቀጥለው የትምህርት ክፍል እንዲቀጥል ያደርገዋል። ሁልጊዜ ተማሪው ያለበት ደረጃ ይታወቃል ማለት ነው።

ይህንንም ለማድረግ ፈጣሪያችን አምላካችን እግዚአብሔር መምህራችንና ተማሪዎቻችንን ባርኮ ትምህርቱን እንዲገልጽላቸው ያድርግልን። አሜን!

Bible Studies for Group 3

They are a part of the calling God has placed within each and every Christian. However, those statements tend to resound a little louder in your ears as a youth believers. It is deeply ingrained in the essence of who you are.

Our church Ethiopian Orthodox Tewahdo Church has a goal for every age to go through the life of Christianity. We are responsible for the kids to go through the life of the Orthodoxy path.

ይህ አማርኛ የሁለተኛ ክፍል ትምህርት ከአንደኛ ክፍል የቀጠለ ሲሆን አዲስ ተማሪዎች ሲመዘገቡ የመጀመሪያውን ክፍል ትምህርት ያካተተ የመግቢያ ፈተና ወስደው፤ ውጤታቸው ከ80% በላይ ከሆነ የሁለተኛን ክፍል ትምህርት መከታተል ይችላሉ።

መምህር፡

ትምህርት የሚሰጥበት ወቅት፡

COURSE DESCRIPTION

Amharic for Group 1 setup for children who started Amharic lessons for the first time. The age for this class starts from 5 years and above who never had experience in  Amharic language in terms of speaking, reading, and writing.

The lessons consist of different sections from the beginning of the first class to the end of year. Each section that offers every week covers from simple to next level by going through each alphabet, getting to know how to pronounce, write, and use them. Students will learn new topics every week.  It is advised that no student should miss any class as it is a continuity of the last class. Before the end of the year, the students will gradually introduce how to construct simple and easy words and sentences.

CERTIFICATION

By the end of the term, students who successfully pass the year courses will receive a passing grade to proceed the Amharic Group 2 lesson plan.

LEARNING OUTCOMES